የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ቤት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን · ካስል

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ቤት

ከፊደል እስከ ቅኔ — ስድስት ደረጃዎች፣ አንድ ጉዞ

ካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዐለም ቤተ ክርስቲያን

የትምህርት ደረጃዎች
፮
17:00 – 18:30
እሑድ
በመስመር ላይ
Zoom
የማጠቃለያ ፈተና
መስከረም

የትምህርት ደረጃዎች

እያንዳንዱ ደረጃ በቀደመው ላይ ይገነባል፤ የዓመቱ ማጠቃለያ ፈተና ወደሚቀጥለው ደረጃ ያሸጋግራል።

  1. ፩
    ደረጃ 1

    ቀዳማይ

    ፊደል

    ዓላማ: ከሀ እስከ ፐ ያሉትን ፊደላት በሰባቱም ቤቶቻቸው ማወቅ፣ መጥራትና መጻፍ።

  2. ፪
    ደረጃ 2

    ካልአይ

    ዓረፍተ ነገር

    ዓላማ: በሁሉም የፊደል ቤተሰቦች ቃላትን ማንበብና መጻፍ፤ አጫጭር ዓረፍተ ነገሮችን መመሥረት።

  3. ፫
    ደረጃ 3

    ሣልሳይ

    የንባብ ቅልጥፍና

    ዓላማ: እስከ ስምንት አንቀጽ ያለውን ጽሑፍ ሥርዓተ ነጥብ ጠብቆ በትክክልና በፍጥነት ማንበብ።

  4. ፬
    ደረጃ 4

    ራብዓይ

    ንባብና መረዳት

    ዓላማ: ማንኛውንም ጽሑፍ በፍጥነት አንብቦ መረዳትና ለሁሉም ዓይነት ጥያቄዎች መልስ መስጠት።

  5. ፭
    ደረጃ 5

    ኀምሳይ

    ጽሕፈትና ሰዋስው

    ዓላማ: ከአንድ እስከ ሦስት አንቀጽ መጻፍ፤ ሞክሼ ፊደላትንና ሰዋስውን በትክክል መጠቀም።

  6. ፮
    ደረጃ 6

    ሳድሳይ

    ብቃትና ቅርስ

    ዓላማ: ምሳሌያዊ አነጋገርን፣ ቅኔንና የግእዝ መሠረታዊ ዕውቀትን መማር፤ በቤተ ክርስቲያን ማንበብ።

የእሑድ መርሐ ግብር

በዙም (Zoom) በኩል በመስመር ላይ

  1. 17:00
    የመክፈቻ ጸሎት፣ መዝሙርና የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ
  2. 17:30
    እያንዳንዱ ተማሪ ወደ ደረጃው ክፍል ይገባል
  3. 18:30
    የትምህርቱ ማብቂያ