እገዛ › 🔑 መጀመሪያ፦ መለያና መድረኩ
መግባትና የይለፍ ቃል ሲረሱ
መግባት፣ የተረሳ የይለፍ ቃል፣ መውጣት።
፬ ደረጃዎች🔗 ወደ ገጹ ሂድ
- 1
school.dqmedhanealem-kassel.com ን ይክፈቱ። ኢሜይልዎን 1 እና የይለፍ ቃልዎን 2 ጽፈው «ግባ» 3 ይንኩ።
- 2
የይለፍ ቃልዎን ከረሱ «የይለፍ ቃሉን ረሱት?» 4 ይንኩ፤ ኢሜይልዎን ጽፈው «አገናኝ ላክልኝ» ን ይንኩ።
💡 በኢሜይል የሚደርሰው አገናኝ ለ፷ ደቂቃ ብቻ ያገለግላል።
- 3
በኢሜይሉ ያለውን አዝራር ነክተው አዲሱን የይለፍ ቃል 5 ሁለት ጊዜ 6 ጽፈው «የይለፍ ቃሉን ቀይር» 7 ይንኩ።
- 4
ለመውጣት ስምዎን ወይም ምስልዎን ይንኩ፤ ከዚያ «ውጣ» 8 ን ይንኩ፤ ለማረጋገጥ እንደገና «ውጣ» ይንኩ።
💡 በጋራ ወይም በሌላ ሰው መሣሪያ ላይ ሁልጊዜ ይውጡ።